
አዲስ አበባ፡ የካቲት 05/2018ዓ.ም (አሚኮ) ለአምስት ወራት የቆየው የአቢሲኒያ ባንክ የዲጂታል ግብይትን የሚያበረታታው “ያልታሰበው ሲሳይ” መርሐግብር ሁሉንም የዲጂታል ግብይት ተጠቃሚ ሰዎችን በዕጣው አካቶ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ በወጣው ዕጣ ለይቷል።
በዚህ መሠረት መሐመድ ከድር ዕድለኛ ኾኗል። ዕድለኛው ዛሬ አዲስ አበባ አያት አካባቢ የሚገኘውን ባለሁለት መኝታ አፓርትመንት ቁልፍ ተረክቧል።
ዕድለኛው መሐመድ ከድር ሀሳቡን ሲገልጽ “ላሳካው በምፈልገው ሕልሜ መካከል ቤት ትልቁ ነበር አቢሲኒያ ባንክም አሳክቶልኛል” ብሏል።
የባንኩ የዲጂታል ግብይት ችፍ ሶስና መንገሻ ባንኩ በዋናነት በዲጂታል ዘርፍ የዲጂታል ሥነምህዳር ሁነት መፍጠር፣ የደንበኛ ዕለታዊ ክንውን በዲጂታል ሁኔታ ላይ መገኘት፣ የተሳትፎ ተግባቦት ሽያጭን ማሳደግ፣ መረጃን መሠረት ያደረገ የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ማድረግ እና እርስ በእርስ የተሳሰረ ውጤታማ የዲጂታል ግንኙነት ላይ እንደሚያተኩር ጠቁመዋል።
ዲጂታል ፋይናንስ ዋናው ዓላማው ርቀትን ማጥፋት፣ በፋይናንስ ተቋማት እና በደንበኞች መካከል የጊዜ እና የርቀትን ክፍተት የሚሞላ ድልድይ መኾኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።
በብሔራዊ ባንክ መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ በዓመት የዲጂታል ገንዘብ ግብይት እና ዝውውር 12 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ደርሷል።
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
