የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።

3
ጎንደር: የካቲት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ሁሴን ጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማቷን በሚገባ እያከናወነች መኾኑን አንስተዋል።
በክልሉ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች የኮሪደር ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ልምድ ልውውጥ ማድረጉ ደግሞ ሥራው እንዲጎለብት ያደርገዋልም ብለዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ የልምድ ልውውጥ መደረጉ በክልሉ የሚገኙ ከተሞች የተፋጠነ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል ነው ያሉት።
የአሁኑ ትውልድ የራሱን ታሪክ እየፃፈ እንደኾነ ያነሱት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ተሻገር አዳሙ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በጎንደር ከተማ ተዘዋውረው ከተመለከቱት የልማት ሥራ ለባሕር ዳር ከተማ የሚኾነውን ተሞክሮ በመውሰድ በሥራ ላይ እንደሚያውሉም አመላክተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ታደሰ የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ከጎንደር ከተማ ታሪክ ቀለም እና ባሕል ጋር መሠረት ተደርጓል ብለዋል። በከተማ እየተከናወነ የሚገኘው 2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተጠናቀቀ መኾኑም ተጠቅሷል።
በ3ኛ ዙር የአራዳ የገበያ ማዕከላት እድሳት እየተከናወነ መኾኑን አንስተዋል። 4ኛው ዙር በቅርቡ እንደሚጀመር ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ‎ተስፋየ ጋሹ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleመሰየም ምንድን ነው?
Next article1 ቢሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ፋብሪካዎች እየተመረቁ ነው።