በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር 142 ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

9
ሰቆጣ: የካቲት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 32ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የአሥፈጻሚውን የስድስት ወራት ዕቅድ ክንውን ይገመግማል።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንታይቱ ካሴ የዋግ ኽምራን ሰላም ለማስጠበቅ እና ሰላሙን ለማጽናት ሲሉ ለተሰው የሰላም አስከባሪዎች የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
ለቤተሰቦቻቸው መቋቋሚያ ድጋፍ እንዲደረግ ያሳሰቡት አፈ ጉባኤዋ የጀግኖች መንደር ለመገንባት የተጀመረውን ተግባር እንደሚደግፉም ጠቁመዋል።
ባለፉት ሰድስት ወራት በዩኤንዲፒ እና በዓለም ባንክ ከ142 ያላነሱ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት መኾናቸውን ገልጸዋል። በፌዴራል እና በክልል በጀት ድጋፍ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተሻለ መንገድ እየተተገበሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ኾኖ እንዲካሄድ ሁሉም አካላት የጋራ ርብርብ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
ዘጋቢ ፦ደጀን ታምሩ
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበሰው የመነገድ ወንጀል እና ተጠያቂነቱ።