“ከ74ሺህ በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል”

7
ደሴ: የካቲት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማ እና የውይይት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ አካሂዷል።
በበጀት ዓመቱ የእንሰሳት በሽታን ከመከላከል አንፃር፣ የአንድ ቀን ጫጩትን በስፋት ለማኅበረሰቡ በማዳረስ፣ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የዓሳ ጫጩትን በማሰራጨት በኩል አመርቂ ሥራዎች መሠራታቸው ተመላክቷል።
የተሠሩ ሥራዎች መልካም ቢኾኑም ዞኖች ካላቸው የእንሰሳት እና ዓሳ ሃብት አቅም አንፃር ቀሪ ሥራዎች እንዳሉም በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስቷል።
ባለፈው ስድስት ወር በእንሰሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት እና ለኢንደስትሪዎች ግብዓት በመኾን ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን የአማራ ክልል እንስሳት እና አሳ ሃብት ቢሮ ኀላፊ ጋሻው ሙጨ (ዶ.ር ) ገልጸዋል።
ቢሮ ኀላፊው ከ126 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታስቦ ከ74ሺህ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
በተለያዩ መስኮች ሰፊ ሥራዎች ቢሠሩም የዶሮ ሃብት ልማትን ከፍ ለማድረግ የአንድ ቀን ጫጩት ምርታማነት ላይ ሰፊ ሥራ የሚጠበቅ መኾኑን ቢሮ ኀላፊው አንስተዋል።
የግብዓት አቅርቦት እጥረትም ሌላው የትኩረት አቅጣጫ መኾኑን ነው የገለጹት።
ከሌማት ትሩፋት እንፃር የተጀመሩ ሥራዎችን ማስፋት እንደሚገባ እና የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትንም ከተለመደው አሠራር በመውጣት በላቀ አፈፃፀም መከወን እንደሚገባም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- አበሻ አንለይ
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦
Next articleበደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ በስድስት ወራት ብቻ ለ48 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል።