“ጎንደር ከተማ የልማት ተጠቃሚ እንድትኾን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ እናመሰግናለን” ወጣቶች

10
ጎንደር: የካቲት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር በከተማዋ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ከወጣቶች ጋር አካሂዷል።
‎”‎በዘመን ሂደት እያሸነፈ የመጣ ከተሜነት” በሚል እሳቤ የጎንደር ከተማ የቀደምት ሥልጣኔ፣ ዘመናዊነት፣ የልማት ሥራዎች እና ነባራዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ የመነሻ ጽሑፍ በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ቀርቧል።
‎በመነሻ ጽሑፉ የጎንደር ከተማ ቀደምት ሥልጣኔን ጨምሮ የቱሪዝም ሃብት እንዲኹም የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት እድሳት፣ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች ተቃኝተውበታል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው የጥምቀት በዓል ጎንደር ከተማ ያላትን የልማት ተጠቃሚነት የተገለጸበት እንደነበር አስተውሰዋል። ለዚህም የወጣቶች አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንደነበር ተናግረዋል።
‎ጎንደር ለበርካታ ዓመታት ከልማት እርቃ መቆየቷን ያነሱት አቶ ቻላቸው ዛሬ ላይ ያገኘችውን የልማት ዕድል በተገቢው መንገድ መጠቀም ይገባልም ነው ያሉት።
ጎንደር ከተማ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልን ጨምሮ የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ፤ የተማሪዎች ምገባ፤ የጤና መሠረተ ልማት እና ሌሎችም መሠረታዊ ነገሮች እንደሚያስፈልጓት አብራርተዋል።
‎በከተማዋ 7 ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ መኾናቸውንም አንስተዋል። ይህንንም ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
‎የከተማዋን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አብረን እንሥራ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በብልጽግና ፓርቲ የጎንደር ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ናርዶስ ቢራራ ለልማት ሥራዎች ውጤታማነት የወጣቶች ሚና ከፍ ያለ መኾኑን ገልጸዋል።
‎የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ጎንደር ያገኘችው የመልማት ዕድል የከተማዋን ገጽታ ያስዋበ እና ወደ ቀደመ ከፍታዋ የመለሰ መኾኑን ተናግረዋል።
‎የጎንደርን የልማት ተጠቃሚነት ፍላጎት ለማሟላት ቀጣይነት እንዲኖረው ማስቻል ይገባል ያሉት ወጣቶቹ ለከተማዋ ልማት እና ሰላም በባለቤትነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ወጣቶቹ ከተማዋ የልማት ተጠቃሚ እንድትኾን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ቃልኪዳን ኃይሌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ቤተ መጻሕፍቱ ትውልድን የሚገነባ ዘመን አይሽሬ ቅርስ ነው” የሰቆጣ ነዋሪዎች
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦