በ2018 በጀት ዓመት ለ1 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

7

ደሴ: የካቲት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ በበጀት ዓመቱ በባለፈው ስድስት ወር ያከናወናቸውን ተግባራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ገምሟል።

በክልሉ ያሉ የሥልጠና ኮሌጆች ብቁ እና በክህሎት የዳበረ ወጣት ከማፍራት አኳያ እየተወጡት ያለው ድርሻ ከፍ ያለ መኾኑን የጠቆሙት የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) በሥድስት ወሩ ለ6 መቶ 25 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።

ከነዚህ ውስጥ ከ420 ሺህ በላይ የሚኾኑት የሥራ እድል የተፈጠረው በሲስተም በተዘረጋ አሠራር መኾኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች በቋሚ እና በጊዜያዊነት የሥራ እድል ለመፍጠር ታቅዷል ያሉት ቢሮ ኀላፊው ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር እና በቅንጅት በመሥራት ዜጎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሥራ እድል እንዲፈጥሩ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

ዘጋቢ:- ሰልሀዲን ሠይድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የዋግ ሕዝብ የጽናት ተምሳሌት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ