
ደሴ: የካቲት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በአዳሜ፣ በገርባ እና ደጋን ከተሞች በ210 ሚሊዮን ብር የተገነቡ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ናቸው ተጠናቀው በዛሬው እለት የተመረቁት።
በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ አጋማሽ 10 የገጠር እና 6 የከተማ ትልልቅ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች እና 250 አነስተኛ የውኃ ተቋማት ተገንብተዋል።
ፕሮጀክቶቹ በአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ፣ በዋን ዋሽ እና በሌሎችም የበጀት ድጋፍ እየተገነቡ መኾናቸው ተመላክቷል።
ዘጋቢ:- አሊ ይመር
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
