የእናቶችን ሕይዎት ለመታደግ የባለሙያዎች እና አጋር አካላት ተሳትፎን ማጠናከር ይገባል።

5

ጎንደር፡ የካቲት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የጤናማ እናትነት ወር የማጠቃለያ መርሃ ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አበበ ተምትም በሀገር ደረጃ ለ39ኛ እና በአማራ ክልል ለ16 ጊዜ ከጥር 01 እስከ ጥር 30/2018 ዓ.ም የጤናማ እናትነት ወር እየተከበረ ይገኛል ብለዋል። ወሩ መከበሩ ባለሙያዎች፣ የሥራ ኀላፊዎች፣ አጋር አካላት እና ማኅበረሰቡ ለእናቶች ልዩ ትኩረት በመሥጠት እንዲሠሩ ለማስቻል መኾኑን ምክትል ቢሮ ኀላፊው ጠቅሰዋል።

በክልሉ የእናቶችን ጤና ለማሻሻል በስድስት ወራት በተሠሩ ሥራዎች ከ300 ሺህ በላይ እናቶች በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።
ከሆስፒታል ባሻገር በ37 ጤና ጣቢያዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መሠጠቱ ተጠቅሷል።

ሕይወት የምትሰጥን እናት ሕይወት ለመታደግ ባለሙያዎች፣ የሥራ ኀላፊዎች ፣አጋር አካላት እና ማኅበረሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በገንዘብ በመደገፍ በተቋማት የሕክምና ግብዓት ለማሟላት ተሳትፎን ማጠናከር እንደሚገባም መልእክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ የእናቶችን ጤና ለመጠበቅ የሴቶች አደረጃጀቶችን በመጠቀም ከግንዛቤ ፈጠራ እስከ ክትትልና ድጋፍ እየሠሩ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።

የእናቶችን ጤና ለመጠበቅ በተሠሩ ሥራዎች ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰው ገና ቀሪ ሥራዎች ይጠበቃሉ ብለዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ከቅድመ እስከ ድህረ ወሊድ ድረስ ክትትል በማድረግ የእናቶችን ጤና መጠበቅ እንደሚገባ አንስተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የእናቶችን ጤና ለመጠበቅ በጤና ተቋማት የወላድ እናቶች ማቆያዎችን ማጠናከር እና ደም ከለጋሾች የመሰብሰብ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- አገኘሁ አበባው

አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለሀገር ሲሉ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልቱ ቤተ መጻሕፍት እንዲኾን ወስነናል” ሌትናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ
Next articleበሰሜን ሸዋ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 250 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል።