በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ የኢንቨስትመንት ፎረም እየተካሄደ ነው።

7

ደብረ ብርሃን: የካቲት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልእክት የአምራች ዘርፉን ለማነቃቃት ያለመ የኢንቨስትመንት ፎረም ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በኢንዱስትሪ ልማት እና በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዋ የምትጠቀሰው የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ይህንን መድረክ ማካሄዷ ለቀጣይ የኢንዱስትሪ ጉዞዋ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ይህ የኢንቨስትመንት ፎረም በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት አካል ነው።

በመድረኩ ከፍተኛ የፌዴራል፣ የክልል እና የሰሜን ሸዋ ዞን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። በከተማዋ በኢንቨስትመንት ከተሠማሩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ያደርጋሉም ተብሏል፡፡

አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመማር ማስተማር እንቅስቃሴውን ለማሳለጥ ጥናቶች መሠረታዊ ናቸው።
Next article“ለሀገር ሲሉ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልቱ ቤተ መጻሕፍት እንዲኾን ወስነናል” ሌትናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ