ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰቆጣ ከተማ የተገነባውን ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

20

ባሕር ዳር: የካቲት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰቆጣ ከተማ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የተገነባውን ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ቤተ መጻሕፍቱ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ለዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ሰማዕታት መታሰቢያ ነው የተገነባው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌትናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ አሰፋ ቸኮል፣ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሥተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገር ዳር ድንበር ከመጠበቅ፣ ሉዓላዊነትን ከማስከበር፣ የሕዝብን ሰላም ከማረጋገጥ ባሻገር በሀገር ልማት ላይም ተሳታፊ ነው።

ከሕዝብ የወጣው ሰራዊቱ ከራስ በፊት ሕዝብ እና ሀገር በሚል መርሑ ለሀገር እና ለሕዝብ ጠበቃ ኾኖ ቆሟል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የቡና ምርትን ለማሳደግ እየሠራ ነው።
Next article“ተተኪ ወጣቶች ላይ መሥራት ለነገ ስፖርት ስኬት መሠረት መጣል ነው” ሚኒስትር ሼዊት ሻንካ