በትምህርት ላይ የደረሰውን ስብራት ለመጠገን በቁጭት መሥራት ይገባል።

4
ደብረ ታቦር፡ ጥር 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ለሁለት ቀና ሲያካሂድ የቆየው የግምገማ መድረክ ተጠናቅቋል።
ባለፉት ዓመታት ተማሪዎች በትምህርት ቤት የመገኘት ቁጥር በተለያዩ ምክንያቶች በመቀነሱ ዕቅዳቸውን ማሳካት አለመቻላቸውን የተናገሩት የፋርጣ ወረዳ የጋሳይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጉድኝት ማዕከል ሱፐር ቫይዘር ሰላም ሞላ ናቸው።
በተያዘው የትምህርት ዘመን በኅብረተሰቡ ቀና አመለካከት እና አንፃራዊ ሰላም በመኖሩ ተማሪዎቹ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ በቁርጠኝነት እየሠሩ እንዳለ ገልጸዋል።
የስማዳ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኅላፊ ሰርክአዲስ ተሻገር እንደ ክልል ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነው መቆየታቸውን አንስተዋል።
የተፈጠረውን የትውልድ ክፍተት ለማጥበብ እና የባከነውን ጊዜ በማሰብ ለታማሪዎች አሰፈላጊውን ዋጋ እንደ ሚከፈሉ አስገንዝበዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኅላፊ ደስታ አስራቴ ባለፉት ዓመታት በትምህርት ላይ የደረሰውን ስብራት ለመጠገን በቁጭት እየሠሩ መኾናቸውን አስገንዝበዋል።
ኀላፊው በተያዘው የትምህርት ዘመን በክልል አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ57 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በጥሩ ውጤት ለማስፈተን በትኩረት ተይዞ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የዶክተርስ አሊያንስ ጄኔራል ሆስፒታል ተመረቀ።
Next article“የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ለአካባቢው ግርማ ሞገስን ያላበሰ፣ ለእኛም ሃሴትን የሞላ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ