
ደብረ ታቦር: ጥር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።
የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የትምህርት መምሪያ ኅላፊ ደስታ አስራቴ ትምህርት የብዙ አጋር አካላትን ተሳትፎ የሚፈልግ ጉዳይ ነው ብለዋል።
በግማሽ ዓመቱ መልካም የትምህርት አፈጻጸም የነበር ቢኾንም እንኳን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ግን በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል። ችግሩን ለመቅረፍ ትልቅ ኅላፊነትን መውሰድ አግባብ ነው ተብሏል። የክልል አቀፍ እና የሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡም ትኩርት እንደተሰጠ በግምገማ መድረኩ ላይ ተነስቷል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ ትምህርት ተኪ የሌለው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሀብት በመኾኑ ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
በገበያ ተወዳዳሪ የሚኾን የሰው ኃይል ለመገንባት የትምህርት ጥራት ታሳቢ ተደርጎ እየተሠራ መኾኑንም መምሪያ ኀላፊው አስገንዝበዋል።
በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ለትምህርት እንቅፋት እየኾኑ እንደኾነም በዕለቱ ተነስቷል።
የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት እና ፍጹም የኾነ ሰላምን ለማምጣት የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
