የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጄክት የተጠቃሚዎችን ኑሮ እያቀለለ ነው።

3

 

ደብረታቦር፡ ጥር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ሥራ ፕሮጄክት የ2ኛ ምዕራፍ 2ኛዙር የአካባቢው ልማት ተጠቃሚዎች የምረቃት ፕሮግራም ተካሂዷል።

የደብረታቦር ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ኤልሳ ደሞዝ በፕሮጄክቱ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ኑሮን ለማሸነፍ ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን የተሻለ ሕይወት እየኖሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።

ሌላኛው ነዋሪ ንጉሴ እንደሻው በአከባቢው ከነበረው ወቅታዊ ሁኔታ እና የኑሮ ውድነቱ ተደማምሮ የቤት ኪራይ ለመክፈል ይቸገሩ እንደነበር ተናግረዋል። አሁን በፕሮጄክቱ ውስጥ ጠንክሮ በመሥራት የተሻለ ሕይወት እየኖሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።

የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ምግብ ዋስትና እና ሴፍቲኔት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዮዮሐንስ ካሴ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ማስመረቅ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ተመራቂዎቹ በአረንጓዴ ልማት፣ በተፈጥሮ ሃብት ሥራ፣ በከተማ ግብርና፣ በደርቅ ቆሻሻ ማስወገድ፣ ከተመዋን ውብና ፅዱ በማድርግ እና በሌሎች ሥራዎች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሥራ እድል ተፈጥሮላቸው መቆየቱን ገልጸዋል።

የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ ተመራቂዎች ሥራ ሳይንቁ ጠንክረው በመሥራት ከዚህ በላይ የስኬት ማማ ላይ መድርስ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ሥራቸውን ትኩረት ሰጥተው ለሚሠሩ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎች እንደሚመቻቹም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየህወኃትን ዳግም ወረራ የሚያወግዝ ሰልፍ በደባርቅ ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next articleየህወኃትን ዳግም ወረራ የሚያወግዝ ሰልፍ በደባርቅ ከተማ እየተካሄደ ነው።