
ደባርቅ: ጥር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ህወኃት ያደረገውን የዳግም ወረራ ሙከራ የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልፉ የሃይማኖት አባቶች፣ የደባርቅ እና አካባቢው የማኅበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በዕለቱም:-
👉 “ኢትዮጵያን ገንብተን እንጂ አፍርሰን አናልፍም!”
👉 “የአማራ ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ይፈልጋል!”
👉 “ህወኃት የሥልጣን እንጂ የሕዝብ ጥያቄ የለውም!”
👉 “መከላከያ ሠራዊታችን ብሔራዊ ኩራታችን ነው!” እና
👉”ጽንፈኝነት የአንድነት ገመድን ይበጥሳል!” የሚሉ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
