የአፋሕድ ከፍተኛ አመራሮች አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ።

6
አዲስ አበባ: ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከመንግሥት ጋር ስምምነት የፈፀሙ የአፋሕድ አመራሮች
በዛሬው ዕለት ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ሊፈቱ ይገባቸዋል ያሏቸውን ጥያቄዎችን አንስተዋል። በጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት አድርገው አጀንዳቸውን በመሰብሰብ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተወካዮቻቸው አስረክበዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አጀንዳቸውን ተረክበዋል። የቀረበውን አጀንዳ በአግባቡ በመሰነድም ለሀገራዊ ምክክሩ እንደሚዘጋጅ አስታውቀዋል። ማንኛውም አጀንዳ አለኝ የሚል አካልም አጀንዳውን ማቅረብ እንደሚችልም ዋና ኮሚሽነሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በትጋት የሚሰሩ ክንዶች ሌማታቸውን አትረፍርፈዋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ