“ባንዳነት ያቆስላል እንጂ አይገድልም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

4

ባሕር ዳር: ጥር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ ውስጥ የሰላም እጦት እንዲኖር ያደረገው ምክንያት ማንኛውም የሃሳብ ልዩነት በኃይል የመፍታት ልምምድ ነው ብለዋል። ልዩነትን በኃይል መፍታት ከጥንት የተጣባን በሽታ ነው ብለዋል።

የባንዳነት አመል ሌላው ችግር መኾኑን አንስተዋል። ባንዳነት ያቆስላል እንጂ አይገድልም፤ ባንዳዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን አቁስለዋለል ነገር ግን መግደል አይችሉም ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ጠላቶች ስጋት ሌላኛው ችግር መኾኑን ገልጸዋል። የችግሮች መመጋገብ የኢትዮጵያን ዕድገት እየገቱ መኖራቸውን ተናግረዋል።

የሀገር ውስጥ ባንዳዎች ከውጭ ጠላቶች ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እንድትወድቅ ከሚፈልጉ ኃይሎች ጋር እንደሚሠሩም ገልጸዋል። የጠላቶች ቋሚ ፍላጎት ሀገርን ማፈረስ እንደኾነም አንስተዋል።

አባቶቻችን በጠላቶች ተፈትነዋል፤ ነገር ግን አስደማሚ ገድል ፈጽመው አልፈዋል ነው ያሉት። ጀግኖች አባቶቻችን ከመንግሥት ጋር ተጣላን ብለው ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር እንደማይሠሩ ተናግረዋል። ከአባቶቻችን የሀገር ፍቅር መማር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ሕልውና ዋና ጉዳያቸው መኾኑንም ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የቤት ችግርን ለመቅረፍ እየተሠራ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር)
Next article“ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን አይችሏትም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር)