“የግብርናው ዘርፍ መጠነ ሰፊ ለውጥ አምጥቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

4

ባሕር ዳር፡ ጥር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው መደበኛ ሥብሠባው በምክር ቤቱ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በግብርናው ዘርፍ በዓመቱ ዕቅድ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት ለማምጣት በዕቅድ ተይዞ ባለፉት ስድስት ወራት 999 ሚሊዮን ኩንንታል ምርት ማምረት ተችሏል ብለዋል። ይህም ከዓመቱ ዕቅድ 78 በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት።

በሰብል ምርት፣ በጥጥ እና በሆርቲ ካልቸር ምርቶች በማምረት የዓመቱን 79 በመቶ መፈጸም ተችሏል ብለዋል።

ትራክተር በ2010 ዓ.ም 4 ሺህ 700 ገደማ ብቻ እንደነበር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን 27 ሺህ 200 ትራክተሮች እንደደረሱም አስረድተዋል

ሀገሪቱ በ2010 ዓ.ም ኮምባይነር 338 ገደማ የነበሯት ሲኾን አሁን ላይ 8 ሺህ 700 ኮምባይነሮች አሏት ብለዋል።

በ2010 ዓ.ም በግለሰብ ደረጃ ጥቅም ላይ የሚውሉ 6 ሺህ ገደማ ፓምፕ የነበሯት ሲኾን አሁን 280 ሺህ ፓምፕ አለ ብለዋል።

ማዳበሪያ ላይም ኮምፖስት የማዘጋጀት ልምምድ እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።

በበጋ እርሻ፣ በሌማት ቱርፋት፣ በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተደማምረው በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል ብለዋል።

የማዳበሪያ አቅርቦትን ከውጭ ከማስገባት ይልቅ በሀገር ውስጥ ለማምረት ዘርፈ ብዙ ሥራ እየተሠራ እንደኾነም ጠቁመዋል።

ግብርናው መጠነ ሰፊ የኾነ ለውጥ እና ዕድገት አምጥቷልም ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛውን የኤ አይ ዩኒቨርሲቲ እየገነባች ነው።
Next article“ኢትዮጵያ ለሕዳሴ ግድብ አንድ ብር እርዳታ አልወሰደችም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)