
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በወልቃይት ወረዳ ወፍ አርግፍ ከተማ ሕወሃት የሚያደርገውን ትንኮሳ የሚቃወም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሕዝባዊ ሰልፉ “አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ሰልፈኞቹ ሕወሃት በአማራ ክልል እያደረገ ያለውን ሕገወጥ ወረራ ተቃውመዋል። እምቢ ለዳግም ባርነት አንወድቅምም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
