
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል ነው። በዓሉ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ መካነ ኢየሱስ ከተማም እየተከበረ ነው።
ከአጎራባች ደጋማ ወረዳዎች ከፈረስም ፈረስ መርጠው የሸለሙ ፈረሰኞች ወደመካነ ኢየሱስ ከተማ ገብተዋል። ለመርቆሬዎስ የደገሱ የመካነ ኢየሱስ ነዋሪዎችም “በሞቴ ብሉልኝ” እያሉ እንግዳ ወዳድነታቸውን እያሳዩ ነው።
ፈረሰኞቹ አሁን ላይ ወደታቦቱ ማደሪያ እየተጓዙም ነው። ከባለግርማው ዴንሳ ተራራ ጥላ ሥር፣ ከቀዝቃዛው የዋንቃ ወንዝ ዳርቻ፣ በለምለሙ አምቦ ሜዳ ላይ ፈረስ እና ፈረሰኞቹ እየተመሙ የሚያሳዩት ትዕይንት ልዩ ነው።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
