የመርቆሬዎስ በዓል በስኬት እንዲከበር ፖሊስ የበኩሉን ዝግጅቱን አጠናቅቋል።

17
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ፖሊስ የማኅበረሰቡን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ እና የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየሠራ መኾኑን የተናገሩት የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር ያለው ዘለቀ ናቸው።
ከዚህ በፊት መምሪያው ከደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከሌሎች የጸጥታ መዋቅር አባላት እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በሠራው ሥራ የጥምቀት እና የልደት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ተደርጓል ብለዋል መምሪያ አዛዡ።
የአካባቢው የሰላም ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱንም ነው የገለጹት።
የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በስኬት እንዲከበር ከሌሎች የጸጥታ አባላት እና ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መሠራቱን ነው የተናገሩት።
በበዓሉ መታደም የሚፈልጉ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ኾኑ አልሚ ባለሃብቶች በማንኛው ጊዜ ወደ ከተማዋ መምጣት እንደሚችሉም አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ከሕልም ወደ እውነት፡ ኢትዮጵያ የቀጠናዊ ብልፅግና ሞተር እና የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል!”
Next article“ኢትዮጵያ የታሪክ እና የባሕል ሀብታም ናት” ባካሪ ሳኛ