
ደብረብርሃን፡ ጥር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት “የእርስዎ እርካታ የባንካችን ስኬት” በሚል መሪ ቃል የደንበኞችን ሳምንት በውይይት አክብሯል።
በውይይቱ ላይ የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር ሮቤል ጨበር እንደገለጹት መድረኩ የደንበኞችን አስተያየት በመቀበል አገልግሎትን ይበልጥ ለማዘመን ያለመ ነው።
ዲስትሪክቱ ባለፉት ስድስት ወራት በ65 ቅርንጫፎቹ በኩል ለ5 ሺህ ደንበኞች 45 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ብድር ማሰራጨቱን ገልጸዋል።
ባንኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በዲስትሪክት ደረጃ ደግሞ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ለማኅበራዊ አገልግሎቶች ወጭ አድርጓል ብለዋል።
ባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትን ማዘመን እና ለ40 ሺህ የግብርና ዘርፍ ደንበኞች አዲስ የብድር ስርጭት መጀመሩንም ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ባንኩ 45 ሚሊዮን ደንበኞች እና 2 ትሪሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ እንዳለው ነው የተገለጸው።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም የብድር አቅርቦቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና በሳይበር ደኅንነት ላይ በትኩረት እንዲሠራ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
