ያደግንበትን ማኅበረሰብ ከዚህ በላይ መበደል አንፈልግም።

25

ባሕርዳር፡ ጥር 23/2018ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አካባቢ በትጥቅ ትግል የነበሩ ታጣቂዎች ለሰላም ገብተዋል።

ታጣቂዎቹ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ከነሙሉ ትጥቃቸው በሰላም ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸው።

የታጣቂዎቹ መግባት በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተደረገ ላለው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ለሰላም የገቡ ታጣቂዎች ለሦሥት ዓመታት በጫካ ኾነን ታግለናል፤ የታገልነው ለአማራ ሕዝብ ነፃነት መስሎን ነበር፤ ነገር ግን ትግሉ የግለሰቦች ቤት መሥሪያ እና የሥልጣን ማራዘሚያ ነው ብለዋል።

ትግሉ መሠረተ ልማትን፣ ንብረት የሚያወድም እና ጥፋት የሚያደርስ መኾኑን ገልጸዋል። የተሳሳተ መንገድ መከተላችንን ተገንዝበን ሕዝባችንን ይቅርታ ለማለት የሰላም አማራጭን ተቀብለናል ነው ያሉት።

ለሕወሃት እና ለውጭ ጠላቶቻችን ተለላኪ በመኾን እና የነሱን ተልኮ በመሸከም ያደግንበትን ማኅበረሰብ መበደል አንፈልግም ብለዋል።

ከሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አሁን ላይ ያደጉበትን ማኅበረሰብ ለመካስ ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአገው ፈረሰኞች ማኅበር የተጣላን በማስታረቅ የተቀማን በማስመለስ እና በመደጋገፍ ሲሠራ የቆየ ነው።
Next article“የፈረስ ባሕል የታሪክ ድልድይ እና የፈረስ መስተጋብር የተቆራኘበት ነው” ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው