
ባሕር ዳር: ጥር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ አየነው መላውን ሕዝብ እንኳን ለአገው የፈረሰኞች በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።
በዓሉ ”የአብሮነት ቅርስ የሰላም ውርስ” በሚል መሪ መልዕክት እንደሚከበር ገልጸው የተጣላን በማስታረቅ፣ የተቀማን በማስመለስ እና በመደጋገፍ ሲሠራ መኖሩን ገልጸዋል።
ማኅበሩ በ1932 ዓ.ም መመሥረቱን ገልጸው ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ኹነቶች ሲከበር መቆየቱን ተናግረዋል። የዘንድሮውን በዓል ለየት የሚያደርገውም በዓሉ በዓለም የቅርስ መዝገብ እንዲመዘገብ ሰነድ ተዘጋጅቶመቅረቡ፣ ለገቢ ማስገኛ ሕንጻ መሥሪያ ቦታ ከእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ማግኘቱ፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሙያ ድጋፍ እንደሚያደርግ እና አድማስ ዩኒየን ወጪውን ለመሸፈን ቃል በገባበት ማግሥት መኾኑን ተናግረዋል።
ማኅበሩ 62 ሺህ 739 አባላት እንዳሉት እና በአደረጃጀት እንደሚመራ ጠቅሰዋል። የየደረጃው ከ6 ሺህ በላይ አሠራሮችም ማኅበሩን እና ሕዝቡን በነጻ እንደሚያገለግሉ ጠቅሰዋል።
ዘንድሮ በዓሉ እንዲከበር እገዛ ላደረጉት ሁሉ አመስግነዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
