ከ193 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ለደንበኞች ማበደሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት አስታወቀ።

10
ደብረ ማርቆስ: ጥር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ሳምንትን ”የእርስዎ እርካታ የባንካችን ስኬት ”በሚል መሪ መልዕክት እያከበረ ይገኛል።
ባንኩ የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ አሠራሮችን ለማሻሻል እየሠራ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ማናጀር አፈወርቅ ሰንደቁ ባንኩ ፈጣን እና ተከታታይነት ያለው የፋይናንስ እድገት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ባንኩ የደንበኞችን ሳምንት ሲያከብር የደንበኞችን ፍላጎት ያማከሉ አሠራሮችን በመዘርጋት የአገልግሎት ጥራትን ለማምጣት የግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሰጥበት ስለመኾኑ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ከ193 ሚሊየን ብር በላይ ለፋይናንስ ተቋማት እና ለግል ዘርፉ የብድር አገልግሎት በመስጠት ደንበኞችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የባንኩ ደንበኞችም ባንኩ በፈለጉት ቦታ ተደራሽ በመኾኑ አመስግነዋል። በቀጣይ የብድር አቅርቦት ውስንነት እና የአገልግሎት መቆራራረጥ ክፍተቶች በመኖራቸው ሊስተካከሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ባንኩ ከሚሰጠው መደበኛ አገልግሎት ባሻገር በተለያዩ ዘርፎች ማኅበራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ በመድረኩ ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በክልሉ እና በፌዴራል መንግሥት የተያዙ ፕሮጀክቶች በልዩ ተነሳሽነት እየተፈጸሙ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)