“ከችግር ለመውጣት ሁሉም አካላት ዕውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ጊዜያቸውን አቀናጅተው መሥራት አለባቸው” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

7
ባሕር ዳር: ጥር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ​የማኅበራዊ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ተቋማቱ ከክልሉ የልማት ፍኖተ ካርታ ጋር የተናበበ ስትራቴጅክ ዕቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸውን እና እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የሥራ ስምምነት መፈራረማቸው ለሥራው መሳካት መሠረት መኾኑን ገልጸዋል።
​ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡት ውጤቶች ተስፋ ሰጭ መኾናቸውን የጠቀሱት አስተባባሪዋ ለአፈጻጸሙ መሻሻል የመሪዎች ቁርጠኝነት ማደግ፣ ግልጽ አሠራሮችን መዘርጋታቸው እና የተከታታይ ሥልጠናዎች መሰጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።
ታላላቅ ሀገራዊ ስኬቶች ለፓርቲ እና ለፖለቲካ ሥራ መነቃቃት መፍጠራቸውን አንስተዋል። ​ የተገኘው ውጤት አበረታች ቢኾንም፣ ከሚጠበቀው የለውጥ ፍላጎት አንጻር አሁንም ሰፊ ክፍተቶች መኖራቸውን አንስተዋል። መሪዎች እና ፈጻሚዎች ከጎታች አስተሳሰቦች በመውጣት እንዲሠሩም አሳስበዋል። ክልሉ ከገጠመው ችግር እንዲወጣ ሁሉም አካላት ሙሉ ዕውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ጊዜያቸውን አቀናጅተው እንዲረባረቡም ጥሪ አቅርበዋል።
ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በቀጣይም የኑሮ ውድነትን፣ ሥራ አጥነትን እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለይቶ መፍታት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተመላክቷል። ከተቋም ሪፎርም አንጻርም ሥራን መሠረት ያደረገ የማበረታቻ እና የተጠያቂነት ሥርዓት እንደሚዘረጋም ተጠቁሟል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleኢትዮ ቴሌኮም በስድስት ወሩ 85 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
Next articleጥንታዊ እና ታሪካዊ የኾነችውን ደብረ ማርያም ገዳም ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ነው።