የደባርቅ-ጃናሞራ መንገድ ግንባታን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

8
ባሕር ዳር: ጥር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሮጄክቱ ከተጀመረ ረዥም ዓመታት ያስቆጠረ፤ ሲጓተት የቆዬ እና የሥራ ተቋራጮች እየተቀያየሩ ከፍተኛ ተጽዕኖ ውስጥ የነበረ ፕሮጄክት ነው።
የአካባቢው ሕዝብ ሲማረርበት የኖረ ቢኾንም በአሁኑ ጊዜ በክልሉ መንግሥት፣ በአካባቢው አሥተዳደር እና በኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር በኩል በተፈጠረ ድጋፍ እና ትብብር በ2018 በጀት ዓመት በልዩ ትኩረት ወደ ሥራ መግባት ችሏል።
ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረው የደባርቅ–ጃናሞራ አስፋልት መንገድ ሎት1 ፕሮጄክት ከ63 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝም ሲኾን በተያዘው በጀት ዓመት እስከ 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ለመሥራት የተሻለ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።
የፕሮጄክቱ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ መሪዎች እና ሠራተኞቹ ከባድ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁመው ለመንገዱ በፍጥነት እና በጥራት መጠናቀቅ በታላቅ ትጋት እየሠሩ መኾኑን የአማራ መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ቢሮ መረጃ ጠቁሟል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመርቆሬዎስ በዓልን በተክሌ አቋቋም ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።