የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፉ የሀገርን ኢኮኖሚ ከመቀየር አኳያ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው።

14

 

ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በስድስት ወራት የታቀዱ የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን አስመልክቶ የጋራ ግምገማ እና ምክክር እያካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና እና አካባቢ ጥበቃ ውኃ ሃብት ቢሮ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከፍያለው ሙላቴ መድረኩ በክልሉ የእንስሳት ሃብት ልማት ላይ የታዩ ስኬቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ፋይዳው የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።

የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ የሀገርን ኢኮኖሚ ከመቀየር፤ የሀገራትን ሕዳሴ እና ብልጽግና ከማረጋገጥ አኳያ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መኾኑን አንስተዋል። በቢሮ ደረጃም የመንግሥትን ትኩረት ሊመጥን የሚችሉ ሥራዎች በስድስት ወሩ ትርኩረት ተሰጥቶ ሢሠራ መቆየቱንም ነው የገለጹት።

አፈጻጸሙም ቀደም ሲል ለአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና እና አካባቢ ጥበቃ ውኃ ሃብት ቢሮ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ምርመራ እንደተደረገበት ጠቅሰዋል። በዚህም ተስፋ ሰጭ አፈጻጸሞች እንዳሉ መመልከታቸውን ነው ያስገነዘቡት።

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተተገበረ ያለ እና ውጤት የታየበት ነው።
Next article“የደንበኞች ሳምንት ባንኩ ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት የበለጠ ለማቀላጠፍ እና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ነው” አቶ አህመድ ሽዴ