
ደብረ ማርቆስ: ጥር 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በተከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል። በግብርና፣ በጤና፣ በኢንቨስትመንት፣ በመልካም አሥተዳደር ሥራዎች አበረታች መኾናቸው ተመላክቷል።
አሁን ላይ በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 79 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠት መቻሉንም በሪፓርቱ ተጠቅሷል።
በዞኑ ለሚገኙ ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እንዲሰማሩ ማድረግ ተችሏል።
የግብርና ሜካናይዜሽን አጠቃቀም በማስፋት እና አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ በማድረግ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ አበረታች ሥራዎች መፈፀማቸው ነው የተገለጸው።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳደሪ ዋለ አባተ በዞኑ ባለፋት 6 ወራት የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም በተለያዩ መስኮች ካለፋት 2 ዓመታት በተሻለ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሠራም አስረድተዋል።
በቀጣይም በዞኑ በትምህርት በመሠረተ ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተመላክቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
