የግልግል ዳኝነት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው ሥርዓት ነው።

18

ባሕር ዳር: ጥር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር “የሕግ የበላይነት እና አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት” በሚል መሪ መልዕክት ያዘጋጀው ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

 

በኮንፈረንሱ እየተሳተፉ ያገኘናቸው በኢትዮጵያ የቲ ደብሊው ኤ(TWA) ፓርትነርስ የሕግ ቢሮ ኀላፊ ልዩ ታምሩ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በግልግል ዳኝነት ላይ ብዙ የኢንቨስትመንት እድሎችን የምትወስድ ናት።

 

ከዚህ በፊት የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሲያደርጉ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶች የሚዳኙት በውጭ ሀገራት ሕጎች መኾኑንም ጠቁመዋል። የውጭ ባለሀብቶች የሚያጋጥሟቸውን አለመግባባቶች ሲፈጠሩ መዳኘት የሚፈልጉት እነሱ በሚፈልጉበት ሀገር ሕግ መኾኑን ጠቁመዋል።

 

ይህንን ተከትሎ እንደ ሀገር በርካታ የሕግ ሪፎርሞች መደረጋቸውን አንስተዋል። ከእነዚህም መካከል የግልግል ዳኝነት አንዱ መኾኑን አንስተዋል። ይህም በዘርፉ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ የሚኾን ነው ብለዋል።

 

የግልግል ዳኝነቱም ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትንም የሚያሳድግ ነው ብለዋል። የኮንፈረንሱ ዓላማም የሚመለከተው አካላት ቁጭ ብሎ በመነጋገር እና ግንዛቤ በመያዝ ተግባራዊ ለማድረግ አቅም የሚፈጥር ስለመኾኑ ገልጸዋል።

 

የባሕላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶችን በባሕላችን መሠረት የውስጥ አለመግባባቶችን በመፍታት ከግልግል ዳኝነት ሥርዓት ጋር አሰናስሎ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተዋል።

 

የግልግል ዳኝነት ሥርዓት መደበኛ እና ዘመናዊ የኾነ ሕግ እና ሥርዓት የተዘጋጀለት እና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው አሠራር ስለመኾኑም ጠቁመዋል።

 

ይህም በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ለሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ተግባራትን ዋስትና በመስጠት ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የሚያስችሉ ስለመኾናቸው ተናግረዋል።

 

ዘጋቢ: አሰፋ ልጥገበው

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየግልግል ዳኝነት ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ለዘላቂ ኢኮኖሚ እድገት ሚናው የጎላ ነው።
Next articleየግልግል ዳኝነት በማንኛውም የንግድ እና ኢንቨስትመንት ውሎች ላይ የሚካተት የአሠራር ሥርዓት ነው።