በሕግ የበላይነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

16

ባሕር ዳር፡ ጥር 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሕግ የበላይነት እና አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለዘላቂ ልማት እና ሰላም ያላቸውን ሚና የሚዳስስ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

ኮንፈረንሱን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት ሲኾን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች እና ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮች እንዲሁም የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት መሪዎች እየተሳተፉበት ነው።

ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሱ ከጥር 16 እስከ 17/2018 ዓ.ም ድረስ “የሕግ የበላይነት እና አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው።

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ኅብረተሰቡ ድጋፉን እንዲያጠናክር ተጠየቀ።
Next articleመዛግብት በአጭር ጊዜ ውሳኔ የሚያገኙበትን ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ ነው።