“የሰላም ስምምነቱ የታጣቂዎችን አመለካከት የቀየረ ነው” ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ

17

አዲስ አበባ: ጥር 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ዓመታት በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት የክልሉን ሕዝብ ለማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳቶች ዳርጎት ቆይቷል።

ግጭቱን ይፈቱ ዘንድ መንግሥት የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ከቆዬ በኋላ የአማራ ክልል መንግሥት እና አፋሕድ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

ይህንን የሰላም ስምምነት ተከትሎም በርካታ የአፋሕድ መሪዎች እና አባላት ወደ ሰላም እየገቡ ይገኛሉ።

ስምምነቱ ኃይልን አዛብቷል፤ “የታጣቂዎችን አመለካከት እና ግንዛቤ ቀይሯል”፤ በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እና በደጋፊዎቻቸው መካከል አካሄዳቸው ስህተት መኾኑንም በግልጽ አሳይቷል ያሉት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ናቸው።

በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የታጣቂ መሪዎች እና አባላት ወደ ሰላማዊ አማራጭ እየገቡ መኾኑ የድርድሩን ስኬታማነት ያሳያል ነው ያሉት።

ታጣቂዎችን ለመቀበል እና ድርድሩን ወደ መሬት ለመተግበር የተለያዩ ተግባራት ከክልሉ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተከናዎኑ መኾኑንም አስታውቀዋል።

ዘጋቢ፦ ኢብራሂም ሙሐመድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በታች ጋይንት ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላም ገቡ።
Next article“ጠንካራ የፖሊስ ሠራዊት በመገንባት በክልሉ ሰላም ላይ ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል” ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር)