
ባሕር ዳር: ጥር 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ገብተዋል።
የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የመጡ ታጣቂዎችን የ10ኛ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለ እና የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርታ ጽህፈት ቤት ኀላፊ መንበረ ክፈተው፣ የሃይማኖት አባቶች እና የወረዳው መሪዎች ተቀብለዋቸዋል።
ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለ ሰላምን የመረጡ የቡድኑ አባላት ስህተታቸው ገብቷቸው ሕዝባቸውን ይቅርታ ጠይቀው በመመለስ ነገ ከመንግሥት ጎን ኾነው ሀገራቸውን ለማገልገል መወሰናቸው ተገቢ ነው ብለዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መንበረ ክፈተው በዞኑ ግዳጁን እየተወጣ ያለው መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገው ተደጋጋሚ ስምሪት እና የተደረጉ ውይይቶች ታጣቂዎች በሰላም እንዲገቡ ማገዙን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
