በደብረ ብርሃን ከተማ ለ5 ሺህ ዜጎች ሥራ ተፈጥሯል።

12
ደብረ ብርሃን፡ ጥር 14/2018ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 48ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ መንግሥቱ ቤተ እንዳሉት የልማት ሥራዎች በተሰጣቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማድረግ እና ለተሻለ አፈፃፀም መዘጋጀት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የነገ ትውልድን እያሰብን መሥራት የውዴታ ግዴታ ነው ያሉት አፈ ጉባኤው ምክር ቤቶች የሕዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ አውራ ተቋም እንደመኾናቸው ይህንን ሥራ የመገምገም እና የማረጋገጥ ሥራዎች ሢሠሩ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የስድስት ወር ዕቅድ እና አፈፃፀም ሪፖርትን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በሪፖርታቸው እንደገለጹት በከተማው ከኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አንፃር 38 ፕሮጀክቶች የግንባታ ሥራ ጀምረዋል።
36 ፕሮጀክቶች ደግሞ ግንባታቸውን ያጠናቀቁ ሲኾን በዚህ ሂደትም ለ5 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
150 ሄክታር መሬት ከ3ኛ ወገን ነፃ በማድረግ ለአምራች ኢንዱስትሪው ፕሮጀክቶች መተላለፋቸውንም ገልጸዋል።
ለኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ጥቅም ላይ ያልዋለ መሬትን ከማስመለስ አኳያ ደግሞ 34 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ተነጥቆ ወደመሬት ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ከመንገድ መሠረተ ልማት አኳያም በከተማው 5 ነጥብ 13 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ሥራ ከተቋራጩ ጋር ውል ተወስዶ ሥራ መጀመሩን አስረድተዋል። ግንባታው በተሻለ ጥራት እና በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቅም ሰፊ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
የከተማውን ኮሪደር ልማት ከማስፋት አኳያም ከበሬሳ ወንዝ እስከ መገንጠያ ሁለት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ ለስድሰት ተቋራጮ ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡
ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትም በአጭር ጊዜ 774 ልዩ ልዩ ግንባታዎች ለኮሪደር ልማት ከ3ኛ ወገን ነፃ ማድርግ መቻሉንም አንስተዋል።
ዘጋቢ፦ወንዲፍራ ዘውዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ክፍተት በአካባቢ እና በሕዝብ ጤና ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው።
Next articleቅንጡ ስማርት ስልክ፤ በተራዘመ ክፍያ የግልዎ ያድርጉ!