በኮምቦልቻ ከተማ ዘመናዊ እና ኹሉን አቀፍ የግብይት ማዕከል ተመረቀ።

14
ደሴ: ጥር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር በአይነቱ እና በመጠኑ የመጀመርያ ደረጃ የኾነው ዘመናዊ እና ኹሉን አቀፍ የግብይት ማዕከል አስመርቋል።
120 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበት ዛሬ የተመረቀው የግብይት ማዕከሉ አምራቹን እና ሸማቹን በቀጥታ ያገናኛል ተብሏል።
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ታስቦ የተሠራው ደረጃውን የጠበቀ የግብይት ማዕከል ለኀብረተሰቡ ጉልህ ድርሻ አለው ነው የተባለው።
ማዕከሉን ያስመረቁት የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ( ዶ.ር) ናቸው።
ዘጋቢ፦ሳሙኤል ኪሮስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበባሕር ዳር ከተማ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ምርጫ ዙሪያ እየመከሩ ነው።
Next article“ግዮን የወንዝ ቅዱስ፤ የሀገር ንጉስ”