
ደብረ ብርሃን: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በርግቢ ጋዲሎ ሜዳ የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከብሯል። በአማራ ክልል አርባአራቱ ታቦታት በአንድ ላይ ወጥተው የጥምቀት በዓል ከሚከበሩባቸው ጥቂት ቦታዎች አንዱ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ጋዲሎ ሜዳ ተጠቃሽ ነው።
ጋዲሎ ሜዳ የተጋድሎና የአርበኝነት ቦታ እንደሆነም ይነገርለታል፤ በዓሉን በቦታው በመገኘት ያከበሩት የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤሊያስ አበበ ጋዲሎ ሜዳ ብዙዎች መስዋዕት ሆነው ሀገር ያጸኑበት፤ የሀገርን አንድነት ሊያናጉ የነበሩ አደጋዎች የተቀለበሱበት ታሪካዊ ቦታ ነው ብለዋል።
ታሪክ ከትቦ እንዳስቀመጠው የመካከለኛው ዘመን እንደነ አጼ አምደጽዮን፣ አጼ ይስሐቅ፣ አጼ ናዖድ፣ አጼ በትረማርያምና አጼ ዘርዓያዕቆብ አይነት ድንቅ ሥራዎችን ከሠሩቦቸው ቦታዎች አንዱ ጋዲሎ ሜዳ እንደሆነ ገልጸዋል።
ጋዲሎ ሜዳ የሀገር ጽናትን በጦርነትና አርበኝነት ብቻ ሳይሆን የጥምቀት በዓልን በጋራ በማክበሯም ትታወቃለች ነው ያሉት።
ይህንን ታሪካዊ ቦታ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
