
ደብረ ብርሃን: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ በተለያዩ ሃይማታዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የመቻቻል እና የአብሮነት ተምሳሌት የኾነችው ደብረ ብርሃን የጥምቀት በዓል ሌላው መገለጫዋ እንዲኾን አሥተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በዚህ ዓመት ከተማ አሥተዳደሩ ለታቦታቱ ማደሪያ የሚኾን አመቺ እና ሰፊ ይዞታ ያለው ቦታን ለሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ማስረከቡን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ ቦታውን በማልማት ጥምቀት ከሃይማኖታዊ አከባበሩ ባለፈ ትልቅ የመስህብ ሃብት እንዲኾን ከተማ አሥተዳደሩ ድርሻውን እንደሚወጣም አቶ በድሉ ገልጸዋል፡፡
የዛሬውን የጥምቀት በዓልን ጨምሮ በቀጣዮቹ ቀናት የሚከበሩ ሃይማኖታዊ የንግሥ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የጸጥታ አካላት እና መላው ማኅበረሰብ እያደረገ ያለው ትብብር እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦በላይ ተስፋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
