ጨለማ ወደ ብርሃን ይቀየር ዘንድ በጸሎት መትጋት ያስፈልጋል።

4
ደብረ ታቦር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በደብረታቦር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባኤያት መጻሕፍት መምህር የኾኑት መምህረ መምህራን በጽሐ አለሙ በዓሉን አስመልክቶ ትምህርት ሰጠዋል።
ጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በውኃ ተጠምቆ የእግዚአብሔር ልጅ መኾን፣ ኃጥያትን መታጠብ እና መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደኾነ ገልጸዋል።
የእግዚአብሔር መጠመቅ አምላካዊ ተገባሩ እንደኾነ ነው የተናገሩት። አዳምን ወደ ቀደመው ክብሩ በጥምቀቱ መልሶታል ነው ያሉት። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት እሱ ሊጠቀምበት ሳይኾን የሰዎችን ጥምቀት ለመባረክ የተደረገ መኾኑንም ተናግረዋል።
“ጨለማ ወደ ብርሃን ይቀየር ዘንድ በጸሎት መትጋት እንደሚያስፈልግም” መልዕክት አስተላልፈዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮነን የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት አስተላላፈዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትናን በመረዳት ሀገርን ዝቅ ብሎ ማገልገል እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ክርስቶስ የተጠመቀው ከኃጥያት እንድንነጻ ነው”
Next articleታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀበሉ።