
ደሴ: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በኮምቦልቻ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
አሁን ላይ በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከወነ ይገኛል።
በዕለቱ “እርሱ ንጉስ ሳለ ራሱን እንደ ባርያ ገለጠ” ያሉት የኮምቦልቻ ከተማ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ የስብከተ ወንጌል ኀላፊ መምህር ኪዳነ ማርያም ናቸው። የጥምቀት በዓል ትህትናን የሚያስተምር በመኾኑ “እርስ በርሳችን በትህትና ልንመላለስ ይገባል” ብለዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው ሁሉንም ነገር በፍቅር እና በትህትና የሚከበር በዓል በመኾኑ ሰዎች ልንዋደድ እና ልንከባበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ጥምቀት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን የእዳ ደብዳቤ ለመቅደድ በዮርዳኖስ የመጠመቁ መታሰቢያ በዓል ነው፡፡
ዘጋቢ:- ሳሙኤል ኪሮስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
