የጥምቀት በዓል በባሕር ዳር እየተከበረ ነው።

3

ባሕር ዳር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በባሕር ዳር እየተከበረ ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓባይ ማዶ ጥምቀተ ባሕር ሥርዓተ ጥምቀቱ በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከናወነ ነው።

 

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ተገኝተዋል።

 

ሥርዓተ ጥምቀቱ እየተከናወነ የሚገኘው በታላቁ የዓባይ ወንዝ ዳርቻ ላይ በተዘጋጀው የጥምቀተ ባሕር ቦታ ነው።

 

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጥምቀት በዓል አከባበር እንዳስደነቃቸው የውጪ ጎብኚዎች ተናገሩ።
Next articleየጎንደር የሥልጣኔ፣ የአንድነት እና የክብር ተምሳሌት በተግባር እየተገለጠ ነው።