የጥምቀት በዓል አከባበር እንዳስደነቃቸው የውጪ ጎብኚዎች ተናገሩ።

4

ባሕር ዳር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከቤልጅየም እና ከፈረንሳይ የመጡት ወይዘሮ አና እና አቶ ሮበርት በባሕር ዳር የጥምቀትን በዓል አከባበር ሲጎበኙ አግንተናቸዋል።

 

እንግዶቹ በኢትዮጵያ በቆዩባቸው ቀናት አስደናቂ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህቦች መመልከታቸውን ገልጸው እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል።

 

በዓመት አንዴ ብቻ በሚገኘው የኢትዮጵያውያን የጥምቀት በዓል በመታደማቸው እድለኛ መኾናቸውንም ነው የነገሩን።

 

የተለያዩ የአከባበር ሥርዓቶችን ተመልክተናል። ትርጉሙን ባንረዳውም የባለሥልጣናትን እና የሃይማኖት አባቶችን ንግግር ተከታትለናል። በዚህም እድለኛ ነን ነው ያሉት።

 

በበዓላቱ አከባበር ተደንቀናል፤ ተደስተናል ያሉት ጎብኚዎቹ ከዚህ በፊትም አራት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ገልጸዋል።

 

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጥምቀት በዓል ጸሎተ ቡራኬ በባሕር ዳር
Next articleየጥምቀት በዓል በባሕር ዳር እየተከበረ ነው።