“ሙሽራ የመሰለች፣ እንደ ንግሥት የታጀበች”

14
ባሕር ዳር: ጥር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሙሽራ የመሰለችው፣ በዘመናት መካከል የደመቀችው፣ በእድሜ ርዝማኔ ያልሸመገለችው፣ ሁልጊዜ አዲስ እና ተናፋቂ የኾነችው፣ እንደ ንግሥት የታጀበችው ጎንደር በጥምቀት ከተራ በዓል ደምቃለች።
ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባሕር እየወረዱ ነው። ሊቃውንት በዝማሬ፣ ምዕምናን በኾታ እና በእልልታ ታቦታቱን እያጀቡ ነው።
ጥምቀት በጎንደር የኢትዮጵያ ጥንታዊ ክብር፣ ታሪክ፣ ባሕል፣ ሃይማኖት፣ እሴት እና ማንነት ከሚገለጽባቸው አካባቢዎች መካከል አንዷ ናት።
ሙሽራ የመሰለችው፣ እንደ ንግሥት የታጀበችው ጎንደር አሁን ድንቁን የጥምቀት ሃይማኖት ሥርዓት እየከወነች ነው።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article”የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ተከተሉት፤ አጅቡት”