በኢትዮጵያ ተጨማሪ 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ 117 ሰዎች ደግሞ አገገሙ።

168

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2012 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 895 የላቦራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 5 ሺህ 689 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ከአንድ እስከ 80 ዓመት ያሉ 73 ወንዶችና 46 ሴቶች ናቸው። በዜግነት ደግሞ 116 ኢትዮጵያውያን እና ሦስት የውጭ ሀገራት ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው በቦታ ሲገለጹ ደግሞ 99 ከአዲስ አበባ፣ ሰባት ከሀረሪ፣ አምስት ከትግራይ፣ አራት ከሶማሌ፣ ሦስት ከኦሮሚያ እና አንድ ከአማራ ክልል መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በአስክሬን ላይ ከተደረገ የላቦራቶሪ ምርምራ አራት ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በሀገሪቱ እስከዛሬ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 98 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል ትናንት 117 ሰዎች (78 ከአዲስ አበባ፣ 35 ከትግራይ ክልል እና 4 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር) በማገገማቸው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 132 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

Previous articleበኩር ጋዜጣ 22/10/2012 ዓ/ም
Next articleለ 68 ቀናት በጽኑ ህመም ውስጥ የነበረው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ አስደናቂ ፍጻሜ!