የምንቃረን ሳይኾን የምንስማማ እንሁን።

2

ባሕር ዳር፡ ጥር 09/2018ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች ወጣቶች እና ማኅበረዊ ጉዳይ ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ ወጣት የመንግሥት ሠራተኞች ጋር በክልሉ የ25 ዓመት አሻጋር እቅድ እና ተጠቃሚነት ዙሪያ ምክክር እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ቁጥራቸው 200 የሚደርሱ በክልሉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት የተውጣጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።

የአማራ ክልል ሴቶች ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዘላለም አረጋ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ የ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ፍኖታ ካርታ እቅድ ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ወጣቶች የሀገር እና የክልል ገጸ በረከቶች ናቸው ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው ወጣቶች ለሀገር ግንባታ አይተኬ ሚና እንደሚጫወቱ ነው ያነሱት። ወጣቶችን ያልያዘ ሀገር እና እቅድ ተጠየቃዊ ነው ነው ያሉት።

ወጣት ሃብት ነው፤ ይህንን ሃብት በጥበብ እና በስክነት፣ በማነጽ እና በመጠቀም ለላቀ ስኬት ማድረስ የሁሉም ድርሻ ሊኾን ይገባል ብለዋል። ወጣትነት ሰላምን፣ እድገትን፣ ልማትን እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁልፍ ሚና እንዳለውም ጠቅሰዋል።

ዓለም ለሠለጠኑት እንጅ በጨለማ በርኖስ አጥልቀው ለሚመላለሱት አትመችም፤ “የምንቃረን ሳይኾን የምንስማማ እንሁን” ነው ያሉት።

ከእውነት እና ውድቀት ጋር ተስማምቶ እቅዱን ለመፈጸም ፍላጎት እና ቅን ልቦና ያስፈልጋል ብለዋል።

እቅዱ ሠርቶ መለወጥን የሚጠይቅ መኾኑን እና ወጣቶች በእቅዱ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ምክክር ማድረግ ማስፈለጉንም አንስተዋል።

ዘጋቢ ፦ ሮዛ የሻነህ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፋይዳ መታወቂያ ለገጠር መሬት ዘመናዊ አጠቃቀም እና አሥተዳደር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።
Next articleባሕር ዳር ከተማ አሥተዳድር በቢኬጅ የተገጣጠሙ ዘመናዊ አውቶብሶችን ተረከበ።