ፋይዳ መታወቂያ ለገጠር መሬት ዘመናዊ አጠቃቀም እና አሥተዳደር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።

1

ባሕር ዳር: ጥር 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ”የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ለገጠር መሬት ባለይዞታዎች” በሚል መሪ መልዕክት የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በግብርና ሚኒስቴር የምግብ ዋስትና ማሥተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ስንታየሁ ደምሴ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የፌዴራል ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመወያያ ጽሑፎች እና ጥናቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ፋይዳ መታወቂያ ለገጠር መሬት ዘመናዊ አጠቃቀም እና አሥተዳደር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።
ዘጋቢ:- ዋሴ ባዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሁሉም በአግባብ እና በሥርዓት ይሁን”ብጹዕ አቡነ አብርሃም
Next articleየምንቃረን ሳይኾን የምንስማማ እንሁን።