“ሁሉም በአግባብ እና በሥርዓት ይሁን”ብጹዕ አቡነ አብርሃም

1

ባሕር ዳር: ጥር 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው።

የበዓሉን አከባበር አሥመልክቶ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ አብርሃም መልዕክት አሥተላልፈዋል።

የጥምቀት በዓል ቤተ ክርስቲያን የሰላም አምላክ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ሰላም እና ፍቅር የምትለምንበት ልዩ በዓሏ መኾኑን ገልጸዋል።

ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉ ነገር በሥርዓት እና በአግባብ ይሁን” እንዳለው የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ ፍቅርን፣ አንድነትን እና ሰላምን በሚገልጽ እና ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ መኾን እንዳለበት አሳስበዋል።

ያለሥርዓት እና ሕግ የሚደረግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያሰጥ አለመኾኑንም ገልጸዋል።

ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ወጣቶች፣ ልዩ ልዩ የጽዋ ማኅበራት፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች እንደየ መንፈሳዊ ድርሻቸው እግዚአብሔርን በማመስገን ታቦታትን በሥርዓት ማጀብ ይገባልም ብለዋል።

በበረከት ፋንታ መርገምን እና ጥላቻን ከሚያመጡ ነገሮች መጠንቀቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አሁን ላይ በዓለ ጥምቀቱ የሚከበርበትን ቦታ የማጽዳት፣ የማስተካከል እና የማስዋብ ሥራ መሠራቱንም ነው የገለጹት። የጥምቅት በዓል በሰላም እንዲከበር እየሠሩ ለሚገኙ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ሁሉም በአግባብ እና በሥርዓት ይሁን”ብጹዕ አቡነ አብርሃም
Next articleፋይዳ መታወቂያ ለገጠር መሬት ዘመናዊ አጠቃቀም እና አሥተዳደር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።