የፋይናንስ እምርታ በኢትዮጵያ

9
ባሕር ዳር: ጥር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል በተሰናዳው እና ስድስት የኢትዮጵያን የፋይናንስ እና የገቢ ሥርዓት በመምራት ላይ ያሉ ዐበይት ተቋማት አፈጻጸም በሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ በሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በፋይናንስ አካታችነት ተጨባጭ እድገት ያስገኙ እና ሰፊ መዳረሻ ያላቸው የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርሞች አካሂዳለች።
ከገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት እስከ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈጻጸሞች እና የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ድረስ የእነዚህ አምስት ዓመታት ክንዋኔ በፋይናንስ ዘርፉ ተወዳዳሪነትን በሚያሳድጉ በመንግሥት ቆራጥ እና ስኬታማ ተግባራት የሚገለጥ መኾኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሥልጡን ሕዝብ እና ሥልጡን ከተማ ለመገንባት ሥልጡን አሥተዳደር ሊኖር ይገባል።