የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

3
ባሕር ዳር: ጥር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 31ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡
‎በጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ጌትነት እውነቱ (ዶ.ር) የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት በርካታ ተግባር እና ኀላፊነቶች ያሉት ሕገ መንግሥታዊ ተቋም ነው ብለዋል።
‎ከተግባራት መካከል በአሥፈጻሚ አካላት ላይ ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ እንደኾነም አንስተዋል። በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በትምህርት መምሪያ፣ በወረዳ ፍርድ ቤት፣ በባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ፣ በሰላም እና ጸጥታ፣ በሚሊሻ ጽሕፈት ቤት እና በአምስት ፖሊስ ጣቢያዎች ክትትል እና ቁጥጥር መደረጉንም ጠቁመዋል።
‎በተደረገው ክትትልም አበረታች ሥራዎች መሠራቱን ነው የገለጹት። አፈ ጉባኤው ከተለያዩ ተቋማት ሀብት በማሰባሰብ የ8ኛ ፖሊስ ጣቢያ የቁሳቁስ ችግርን ለመፍታት ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።
‎በምክር ቤቱ ውስጥ ያሉ ኮሚቴዎች ተግባራትን በየጊዜው ሲገመግሙ መቆየታቸውን ገልጸው በዚህም አበረታች ውጤቶች ታይተዋል ነው ያሉት። ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አፈ ጉባኤው የምክር ቤት አባላትም ለከተማዋ ልማት እና ሰላም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎ምክር ቤቱ በውሎው የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ፣ የወረዳ ፍርድ ቤት እና የትምህርት መምሪያን የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸምን ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
‎ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሰው ሠራሽ አስተውሎት እና እግር የኳስ ጨዋታ ዳኝነት
Next article“መንግሥት አሁንም በሩን ለሰላም ክፍት አድርጎ እየሠራ ነው” ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ