
ደሴ: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በውይይቱ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ አገልግሎት ሠጭ ተቋማት እና ወጣቶችም ተሳትፈዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ አባ ለይኩን ወንዲፍራው ከከተራ ጀምሮ እስከ አስተርዮ ማርያም ያሉ የአደባባይ በዓላትን እንደከዚህ ቀደሙ በሰላም ማክበር ያስፈልጋል ብለዋል።
ምዕመናንም በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሠረት በዓላቱን ማሣለፍ ይገባቸዋል ብለዋል።
የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ ሀሰን ሀሚዲን እና የደሴ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓስተር ሰለሞን አበጋዝ በጥር ወር የሚከበሩ ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላትን በመከባበር እና በፍቅር ማሣለፍ የወሎ ማኅበረሰብ የቆየ እሴት መኾኑን አንስተዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሠይድ አሊ የጥር ወር በዓላት የማኅበረሰቡን መልካም መሥተጋብር በተግባር ማሳያ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።
ይህንን መልካም እሴት ወደ ትውልድ ለማሸጋገር በትጋት መሥራት እንደሚገባ አብራርተዋል።
አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ከወትሮው በተለየ በበዓላት ወቅት ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው የገለጹት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ የሃይማኖት አባቶችም ምዕመኖቻቸው ከከፋፋይ አጀንዳ እንዲጠበቁ መሥራት ይገባቸዋልም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ሕይወት አስማማው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
