አሚኮ ለሰላምና ለልማት ከፊት ተሰልፎ የሚሠራ ተቋም ነው።

4
ገንዳ ውኃ: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ ጎንደር ስቱዲዮ ሥራ የጀመረበትን 1ኛ ዓመት አስመልክቶ የገንዳ ውኃ ከተማ ነዋሪዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
አሚኮ ጎንደር ስቱዲዮ ሥራ ከጀመረ አንስቶ ከሕዝብ ጎን በመኾን በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ዘርፍ ብዙ ሥራዎችን በማከናወን አያገለገለ ያለ ተቋም መኾኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አሚኮ በችግሮች ሳይታጠር ታች ድረስ በመውረድ እና ከፊት በመሰለፍ አካባቢውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ሰላምን በማስፈን ማኅበረሰቡ ተረጋግቶ እንዲኖር በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል።
አካባቢው የልማት ቀጣና በመኾኑ ከበፊቱ በተሻለ ሚዲያው የማስተዋወቅ ሥራዎችን እንዲሠራም ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እያሱ ይላቅ አሚኮ በአካባቢው ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል። ከልማት ሥራዎች አኳያም ሰፊ ተግባራት አከናውኗል ነው ያሉት።
የማኅበረሰቡን ወግ፣ ልማድ፣ እሴት እና ባሕል በመዘገብ እና በማስተዋወቅ በኩልም የራሱን አሻራ ያስቀመጠ የመገናኛ ብዙኀን ተቋም መኾኑን አንስተዋል።
የቱሪዝም ዘርፉን ከማነቃቃት አንፃር በርካታ ተግባራትን ያከናወነ መኾኑንም ጠቁመዋል።
ሚዲያው በተለይ የኢትዮ-ሱዳንን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል የሕዝብ ለሕዝብ ዘገባዎችን በተለመደው ትጋቱ እንዲሠራ ጠይቀዋል።
አሚኮ የምዕራብ ጎንደር ዞን ቅርንጫፉን ለማስፋፋት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የዞኑ አሥተዳደርም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያድርግ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአሚኮ ለሰላምና ለልማት ከፊት ተሰልፎ የሚሠራ ተቋም ነው።
Next articleማዳኣ የተባለውን የአፋር ባሕላዊ ሕግ በዩኒስኮ ለማስመዝገብ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።