የአጼ ቴዎድሮስ የልደት በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው።

9
ባሕር ዳር: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የንጉሠ ነገሠት አፄ ቴዎድሮስ 207ኛ ዓመት የልደት በዓል በጎንደር ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
አጼ ቴዎድሮስ ከጎንደር ቋራ ተነስተው የኢትዮጵያን ታላቅነት እና አንድነት ለማጽናት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግና መሪ ነበሩ።
ቴዎድሮስ ትውልዱ ለሀገሩ አንድነት ፣ሉዓላዊነት፣ ከብር እና ኩራት እንዲሠራ ታላቅ አርዓያ ናቸው።
ከዘመናቸው የቀደሙት ቴዎድሮስ አፍሪካ በጨለማ በነበረችበት ዘመን በሀገራቸው ላይ የመጀመሪያው ፋብሪካ ያቋቋሙ፣ የጦር መሣሪያ የሠሩ፣ ከመዘናቸው የቀደሙ ባለ ራዕይ መሪም ነበሩ። ለሀገራቸው አንድነት እና ሥልጣኔ ባበረከቱት አስተዋጽኦ፣ በጀግንነታቸው ሲወሱ የሚኖሩት አጼ ቴዎድሮስ ታሪካቸውን በሚዘክር መልኩ የልደት በዓላቸው እየተከበረ ነው።
ጥር 06 የሚከበረው የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ጥምቀትን በጎንደር አንዱ አካል የኾነና ለጎንደር ከተማ ተጨማሪ የቱሪዝም ሃብት ነው።
ዘጋቢ:- በሪሁን ሽፈራው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየአጼ ቴዎድሮስ የልደት በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው።
Next articleአሚኮ ለሰላምና ለልማት ከፊት ተሰልፎ የሚሠራ ተቋም ነው።